አሁን ላይ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ካሜራዎች እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂዎች በፎቶ ላይ በግልጽ የማይታዩ የጣት አሻራዎችን በማጥራት መልሶ መገንባት የሚያስችል አቅም መፍጠራቸው ተሰምቷል፡፡
በተለይም ከ1.5 ሜትር ባነሰ ርቀት የሚነሱ የቅርብ ፎቶዎች የጣት አሻራን ሙሉ በሙሉ ለማውጣት እጅግ አመቺ ሲሆኑ፣ እስከ 3 ሜትር ባለው ርቀትም ቢሆን የጣት አሻራን በከፊል ማግኘት እንደሚቻል ተረጋግጧል።
ይህ ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስጋትን የፈጠረ ቢሆንም አንዳንድ ባለሙያዎች ግን የሰውን አሻራ ሰርቆ የባዮሜትሪክ መቆለፊያዎችን ለመስበር እንደ መብራት ሁኔታ እና የምስሉ ጥራት ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነገሮች ስላሉ ሂደቱ ያን ያህል ቀላል እንዳልሆነ ይገልጻሉ።
ይሁን እንጂ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ የ ‘V’ ምልክት ያለባቸውን ፎቶዎች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከመለጠፍ በፊት የጣቶቹን ጫፍ በዲጂታል ዘዴ ማደብዘዝ ወይም የጣት መስመሮቹን ማለስለስ እንደሚገባ ባለሙያዎቹ ስለመግለፃቸው ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ግንቦት 04/2018 ዓ.ም
