ሕግ ጥሰው የሚገኙ ኤጀንሲዎች ፈቃድ እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተባለ

ሕግ ጥሰው የሚገኙ ኤጀንሲዎች ፈቃዳቸውን እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድባቸውና በአሁኑ ወቅትም በምርመራ ሂደት ላይ ያሉ ኤጀንሲዎች እንዳሉ ተጠቁሟል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅና ሕገ-ወጥ የሰው ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል አዲስ የዲጂታል አሰራር መዘርጋቱን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩእንዳመለከተው፤ ‹‹ኢ.ኤል.ኤም.አይ.ኤስ›› የተሰኘው ይህ አዲስ የሥራ ስምሪት መረጃ ሥርዓት ዜጎች ከገጠር እስከ ከተማ ያላቸውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና በሕጋዊ መንገድ ወደ ውጭ የሚሄዱበትን ሂደት ለማሳለጥ ይረዳል።

በተጨማሪም የኤጀንሲዎችን እንቅስቃሴ በቅርብ ለመከታተል የሚያስችል የባዮሜትሪክስ መረጃ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉ ተገልጿል።

ይህ አዲስ አሰራር ቀደም ሲል ይወስድ የነበረውን ረጅም ጊዜ በማሳጠር፤ ዜጎች በ30 ቀናት ውስጥ የሥራ ስምሪት ሂደታቸውን እንዲያጠናቅቁ ያስችላል ተብሏል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ግንቦት 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *