የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ በግል እና በትንሽ እርሻ ላይ ሲያርሱ የነበሩ አርሶአደሮች ለኩታ ገጠም አስተራረስ በፍላጎት እንዲደራጁ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የክላስተር አስተራረስን እንደ አማራጭ ተደርጎ ስራ መጀመሩን ያስረዱት ዶ/ር ማንደፍሮ በተሻለ ደረጃ የተገኙ የኩታገጠም አርሶአደሮች እነዚህን ኩባንያዎቹ እንዲመሠረቱ ተደርጓል ብለዋል።
የኩባንያዎቹ መሠረተ ልማት መጀመሩን አያይዘዉ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ሼዶችን ጨምሮ አስፈላጊ ግንባታዎች መጀመራቸውን ተናግረዋል።
በተማረ የሰዉ ሀይል የሚመራ ግብርና እንዲኖር በማድረግ የምርት እሴት መጨመርን ለማበረታታት የቢዝነስ ኘላን እንደሚሰራ ተነግሯል።
በዚህ ዉስጥ መሬታቸዉን ያሰባሰቡ እና እንዲዋሀዱ ያደረጉ አርሶአደሮች በራሳቸዉ መስራትም ወይም ከግብርና ዉጪ የተሻለ ማግኘት እንዲችሉ ሰዎችን ቀጥረዉ እንዲሰሩ ይደረጋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ ” እኛ ሀገር ላይ መተዉ የሚሰሩ አለምአቀፍ ኩባንያዎች በዚህ መልክ የተቋቋሙ ናቸዉ” ሲሉ አስረድተዋል።
ቁምነገር አየለ
ግንቦት 05/2018 ዓ.ም
