ፑቲን በቅርቡ በቻይና ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቅርቡ በቻይና ጉብኝት እንደሚያደርጉ ክሬምሊን አስታውቋል።

በሩሲያ መንግሥት የሚደገፈው አርቲ (RT) እንደዘገበው ከሆነ፣ ለጉብኝቱ የተቆረጠ ቀን ባይኖርም የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሁሉም ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

ፑቲን ለመጨረሻ ጊዜ ቻይናን የጎበኙት በመስከረም ወር 2025 (እ.ኤ.አ) ቤጂንግ ባካሄደችው ታላቅ ወታደራዊ ትርኢት እና ጉባኤ ላይ ለመታደም ነበር።

የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ቀደም ብለው እንደዘገቡት ከሆነ ጉብኝቱ በሚቀጥለው ሳምንት ሊከናወን ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

ግንቦት 06/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *