የዓለም መረጋጋት የሁላችንም የጋራ ፍላጎት ነው – ማርኮ ሩቢዮ በኃያላኑ መሪዎች ወሳኝ ግንኙነት ዙሪያ ጠንከር ያለ መግለጫ ሰጡ

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ በዓለም ዙሪያ መረጋጋትን ማረጋገጥ የማንኛውም ወገን ቀዳሚ ፍላጎት ሊሆን እንደሚገባ አሳሰቡ።

ሚኒስትሩ ይህን መግለጫ የሰጡት፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግን ታሪካዊ ስብሰባ አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

ሬውተርስ የቻይናውን ሲሲቲቪ (CCTV) ዘገባ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ማርኮ ሩቢዮ በሁለቱ ኃያላን አገራት መሪዎች መካከል የሚደረጉ ንግግሮች ለዓለም አቀፍ ሰላም መከበር ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን በአፅንዖት ገልጸዋል።

ይህ የሩቢዮ መግለጫ፣ አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት በምን መልኩ ሊመራው እንደሚችል ፍንጭ የሰጠ ሲሆን፣ የዓለምን መረጋጋት የመጠበቅ ኃላፊነት የጋራ መሆኑን በይፋ ያመላከተ ነው ተብሏል።

ልዑል ወልዴ

ግንቦት 06/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *