የሩሲያ ጠፈር ኤጀንሲ ገቢውን ለማሳደግ በሮኬቶች ላይ ማስታወቂያ መለጠፍ ጀመረ

​የሩሲያ ብሔራዊ የጠፈር ኤጀንሲ (ሮስኮስሞስ) የገጠመውን የበጀት እጥረት ለመቅረፍ በሮኬቶቹ ላይ የንግድ ማስታወቂያዎችን ማስተናገድ ጀምሯል።

ባለፈው ዓመት በፓርላማው በጸደቀው ሕግ መሠረት፥ ኤጀንሲው እንደ ፒ.ኤስ.ቢ ባንክ እና ኮፌማኒያ ካሉ የአገር ውስጥ ተቋማት ጋር የመጀመሪያውን የማስታወቂያ ስምምነት አጠናቋል።

​ናሳ የመንግሥት ተቋም በመሆኑ ራሱን ችሎ ገቢ ማመንጨት አይፈቀድለትም። እንደ ስፔስኤክስ ያሉ የግል ኩባንያዎች ደግሞ የሮኬት መፈንዳት አደጋ ስላሳሰባቸው፥ ስማቸውና አርማቸው ከውድመት ጋር እንዲያያዝ እንደማይፈልጉ ተገልጿል፡፡

​በአንጻሩ ሩሲያ ከዚህ ዓመት ጥር ጀምሮ ማስታወቂያዎችን በመለጠፍ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሩብል በማግኘት ላይ ትገኛለች።

የማስታወቂያው ዋጋ የሚሰላው እንደ ይዘቱ ስፋትና የቆይታ ጊዜ ሲሆን፥ ዋና ዓላማውም ቀጥተኛ ሽያጭ ሳይሆን ከፍተኛ ትኩረት የሚስብ የሕዝብ ግንኙነት  መፍጠር ነው።

​ኤጀንሲው እስካሁን ከባይኮኑር የጠፈር ጣቢያ ማስታወቂያ የያዙ አራት ሮኬቶችን አስወንጭፏል።

 ቀደም ሲልም በ2001  ፒዛ ሃት ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ በመክፈል አርማውን በሮኬት ላይ አስቀርጾ ወደ ዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ፒዛ ማድረሱ የሚታወስ ቢሆንም፥ ድርጊቱ ግን ለዚያ ጊዜ ብቻ የተደረገ ብቸኛ ክስተት ነበር።

ሐመረ ፍሬው

ግንቦት 11/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *