የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከቴራፔይ ኩባንያ ጋር የዓለም አቀፍ የሀዋላ አገልግሎት አስጀመረ

በአፍሪካ ታላላቅ የገንዘብ ዝውውር ከሚከናወንባቸውና በዓመት ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ከሚያስገኙ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ይህን መሰል ዘመናዊ የክፍያ ስልቶች ማስፋፋት ወሳኝ መሆኑም ተመልክቷል።

 ባንኩ የወሰደው ይህ ታላቅ እርምጃ ከአውሮፓ በዩሮ ተመን የሚላኩ የገንዘብ መልዕክቶችን ከቴራፔይ ድንበር ተሻጋሪ ዓለም አቀፍ ክፍያ ኔትዎርክ ጋር በማገናኘት በኳንተም ክፍያዎች ዩሮን መሰረት ባደረገ የክፍያ ስልት በማሳለጥ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክን ሀገር አቀፍ ሰፊ ተደራሽነት በመጠቀም፣ የገንዘብ መልዕክቶችን ማስተላለፍ የሚያስችል መሆኑ ታውቋል።

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደርቤ አስፋው፣ “በዚህ ትብብር አማካኝነት፣ ባንካችን እንደ መሪ ዲጂታል ባንክ ያለውን ሚና በማጠናከር፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፈጣን እና ሙሉ በሙሉ ሕጋዊ የሆነ የረሚታንስ አገልግሎት እያቀረበ ሲሆን የፋይናንስ አካታችነትን እና በመላ ሀገሪቱ አስተማማኝ የፋይናንስ መፍትሄዎችን ተደራሽነት እያሰፋ ነው” ብለዋል።

 የቴራፔይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምበር ሱር’ በበኩላቸው፣ ይህ ትብብር ለዲያስፖራ የገንዘብ መልዕክቶች ፈጣንና የተሻለ አስተማማኝነት ያለው መሠረተ ልማት እንደሚያቀርብ ሲናገሩ ወደ ሌሎች ዓለም አቀፍ መስመሮችም ሊሰፋ እንደሚችል ገልጸዋል።

ይህ ትብብር በ‘Inclusive Financial Technology Foundation’ ድጋፍ የሚካሄድ ሲሆን፣ ተቋሙም ይህ ፕሮጀክት የድንበር ተሻጋሪ የክፍያ መሠረተ ልማትን ለማዘመን እና በታዳጊ ገበያዎች የፋይናንስ አካታችነትን ለማስፋት መሠረት እንደሚጥል ታምኗል።

 የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ፣ 223.48 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ሀብት፣ ከ16 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እና በመላው ሀገሪቱ ከ 700 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት በሀገሪቱ ከሚገኙ የግል ባንኮች አንዱ ነው፡፡

ግንቦት 11/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *