ሩቢዮ ከኢራን ጋር  ‘ጥሩ’ ስምምነት ላይ ሊደረስ እንደሚችል ተናገሩ 


የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጦርነት ለማቆም የሚያስችል ስምምነት ሰኞ ዕለት ሊደረስ ይችላል ማለታቸው ተዘግቧል።
 
በህንድ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ሩቢዮ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት  ንግግሩ “አሁንም በሂደት ላይ ያለ ሥራ ነው” ብለውታል ።
 
ሩብዮ ይህንን ያሉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ስምምነቱ መቃረቡን ጠቁመው የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ ግን ተደራዳሪዎች “በስምምነት ላይ እንዳይቸኩሉ” መመሪያ መስጠታቸውን ከተናገሩ በኋላ ነው።
 
እየወጡ እንዳሉት መረጃዎች ከሆነ ስምምነቱ የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ማራዘሚያን፣ የሆርሙዝ የባህር በር እንደገና መከፈትን እና የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር በተመለከተ ለሚቀጥሉ ድርድሮች የሚሆን ዕቅድን ያካተተ ነው።
 
ስምምነቱ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን ተከትሉ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ሲሆን፣ የእስያ የአክሲዮን ገበያዎች ደግሞ ሰኞ ዕለት ጭማሪ አሳይተዋል።
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ  ሰኞ ዕለት በህንድ መዲና ዴልሂ በነበራቸው ቆይታ “አሁንም በሂደት ላይ ያለ ሥራ ነው። ቀደም ሲል እንደተናገርኩት፣ ታውቃላችሁ ትናንት ምሽት የተወሰነ ዜና የምናገኝ መስሎን ነበር። ምናልባት ዛሬ ሊሆን ይችላል” ብለዋል።
 
ሩቢዮ “ነገሩን ከመጠን በላይ አታጋንኑት” በማለት ማስጠንቀቂያ ቢሰጡም  “ከኢራን ምላሽ ለመስማት ጥቂት ጊዜ ይወስዳል” ሲሉ ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
 
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *