ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቡና 2.3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተነግሯል

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ እንደገለጹት፣ ዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ መቀነስ እና የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት በላኪው ምርት መጠን ላይ አሉታዊ ጫና ፈጥረዋል።

ይሁን እንጂ በበጀት ዓመቱ ከቡና ውጭና ከቡና ሽያጭ የተያዘውን የ3 ቢሊዮን ዶላር ዕቅድ ለማሳካት ሀገሪቱ ውጤታማ ስትራቴጂዎችን ተጠቅማለች።

ዓለም አቀፍ የዋጋ መዋዠቅ የሚታይባቸውን ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸውን ቡናዎች ከገበያ በማስወጣት፣ ጥራት ላይ ትኩረት ተደርጓል። ይህም በቶን የሚገኘውን ዋጋ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ10% እንዲጨምር አድርጓል።

የዓለም የቡና ዋጋ በ32% በቀነሰበት ሁኔታ፣ የኢትዮጵያ ቡና በ33% ከፍ ባለ ዋጋ እየተሸጠ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት አንድ ቶን የኢትዮጵያ ቡና በአማካይ እስከ 6,500 ዶላር እየተሸጠ ነው።

[ሦስት ቢሊየን] ዶላሩ ላይ እንግዲህ እንደምንም እንገባለን መጠኑን ትንሽ ሊያስቸግረን ይችላል።

አሁን ላይ ወደ ሁለት መቶ ሶስት ቢሊየን አካባቢ ደርሰናል በሚቀሩት ሁለት ወራት ላይ ደግሞ ቀረውን እናሳካለን ሲሉ ዶ/ር አዱኛ ደበላ ተናግረዋል፡፡


ግንቦት 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *