ሄዝቦላህ የተኩስ አቁሙን አልቀበልም ማለቱን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ

ሊባኖስ እና እስራኤል የደረሱበትን የሰላም ስምምነት ሄዝቦላህ እንደማይቀበል ማስታወቁን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ።

የዛሬው የዋጋ ንረት የታየው የኦማን ነዳጅ መጫኛ አካባቢ ፍንዳታ በመነሳቱ የነዳጅ ጭነት ከመቋረጡ ጋር በተያያዘም ጭምር ነው።

እስራኤል እና ሊባኖስ ከዚህ ቀደም የደረሱበትን የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚያድሱ ከማስታወቃቸው በተጨማሪ በሊባኖስ ውስጥ የሄዝቦላህ እንቅስቃሴ የሚገደብበት የደኅንነት ቀጣና ለመፍጠርም ተስማምተዋል።

ሄዝቦላህ ግን ስምምነቱን ለሊባኖስ ‹‹አሳፋሪ እና እርባና ቢስ›› በሚል እንደማይቀበለው አስታውቋል።

የሄዝቦላህ መሪ ‹‹ሄዝቦላህ ተኩስ አቁሞ ተዋጊዎቹን ከደቡብ ሊባኖስ የሚያስወጣበት ስምምነት የመሸነፍ ያህል ነው፤ የእስራኤልንም ዓላማ ያሳካል››ማለታቸውም ተዘግቧል።

ግንቦት 28/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *