አቢሲኒያ ባንክ በ‹‹አቢሲኒያ ቪዛ 2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ››ዕድለኛ ለሆኑ ደንበኞቹ ሽኝት አደረገ

አቢሲኒያ ባንክ ከቪዛ ዲጂታል ጋር በመተባበር ‹‹አቢሲኒያ ቪዛ 2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ›› ባካሄደው የሽያጭ ዘመቻ ባለዕድል ሆነዉ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ወደ አሜሪካ ለሚጓዙ ደንበኞቹ የሽኝት መርሐግብር አካሂዷል።

የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች፣ የቪዛ ኢትዮጵያ ተወካይ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች እና የስፖርት ተንታኞች ተገኝተዋል።

ባንኩ መርሐ ግብሩን ከፈረንጆቹ መጋቢት 9 እስከ ሚያዝያ 15 የባንኩን ቪዛ ካርድ ተጠቅመው በፖስ ማሽኖች ላይ ከብር 1 ሺህ ጀምሮ ግብይት ለፈፀሙ ደንበኞች ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል።

ለዕድለኞችም በስፍራው ተገኝተው ውድድሩን እንዲመለከቱ የደርሶ መልስ የጉዞ ትኬት፣ የአራት ቀናት የሆቴል ቆይታ እና የስታዲየም የመግቢያ ትኬት መሸለሙን ገልጿል።

ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በኳታሩ የዓለም ዋንጫ እና በካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ዕድለኛ ደንበኞቹን በዕጣ በመለየት ስፖርታዊ ውድድሮችን በአካል እንዲታደሙ ማድረጉ የሚታወስ ነዉ፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ግንቦት 28/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *