ትራምፕ እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም ስምምነት ተፈራረሙ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የኢራኑ ማሱድ ፔዜሽኪያን ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችል የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ባለ 14 አንቀጽ በሆነው በዚህ የመግባቢያ ሰነድ መሠረት ሁለቱም ወገኖች በሚቀጥሉት 60 ቀናት ውስጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተጨማሪ ንግግሮችን ለማድረግ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል፡፡

በስምምነቱ ላይ እንደተጠቀሰው ይህ የጊዜ ገደብ “በሁለቱም ወገኖች ፈቃድ ሊራዘም የሚችል” ነው።

ይህ ስምምነት የሆርሙዝ ሰርጥን ድጋሚ መክፈት፣ ለኢራን መልሶ ግንባታ የሚውል የ300 ቢሊየን ዶላር ዕቅድን እና አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለቻቸውን ማንኛውንም ዓይነት ማዕቀቦች እንድታነሳ የሚሉ ነጥቦችን ያካተተ ነው፡፡

ኢራን የስምምነቱን ውሎች እንድታከብር ያስጠነቀቁት ትራምፕ፤ ረቡዕ ዕለት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት አማኑኤል ማክሮን በቨርሳይ ቤተ መንግሥት ባዘጋጁት የእራት ግብዣ ላይ የሰነዱን ቅጂ ሲፈርሙ በምስል ተቀርጸዋል።

የአሜሪካ እና የኢራን ተወካዮች የሚገኙበት ይፋዊ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ዓርብ ዕለት በስዊዘርላንድ እንዲካሄድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ይህ ሥነ ሥርዓት ስለመካሄዱ እስካሁን ግልጽ የተደረገ ነገር የለም።

ሀና ሰይፉ

ሰኔ 10/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *