በኢትዮጵያ እና በአየርላንድ መካከል የባህል ዲፕሎማሲን ለማጠናከር አዲስ የቴአትር ስራ ሊቀርብ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴአትርና ባህል አዳራሽ ከአየርላንድ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ‹‹አሉ›› የተሰኘ አዲስ የቴአትር ስራ ለተመልካች ሊያቀርቡ መሆኑን አስታወቁ።

ይህ የቴአትር ስራ በአየርላንድ ታሪክ ትልቅ ቦታ ያለውና በደብሊን አቢይ ቴአትር ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው ሲፔርድንግ ዘ ኒዉስ የተሰኘው ድራማ ትርጉም እንደሆነ ተገልጿል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የአየርላንድ ኤምባሲ የባህል ዲፕሎማሲ ስራ አስኪያጅ ስቴፈን እንደገለጹት፤አየርላንድ የቅዱሳንና የምሁራን ምድር ከመሆኗ ባለፈ ታሪክን በመተረክ የምትታወቅ ሀገር ናት ብለዋል።

ይህ ቴአትር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የባህል ግንኙነት ከማጠናከሩ ባለፈጥበብን እንደ ‹‹ለስላሳ ኃይል›› በመጠቀም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

ቴአትሩ በሚቀጥለው ሳምንት ዕሮብ በሀገር ፍቅር ቴአትር በይፋ መመረቅ እንደሚጀምርም ተነግሯል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሰኔ 12/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *