በቬንዙዌላ የደረሰ ሀይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ ተገለጸ

ከ700 በላይ ሰዎችን አቁስሏል ተብሏል

በደቡብ አሜሪካዋ አገር ቬንዙዌላ ውስጥ በተከሰቱ ሁለት ተከታታይ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጦች ቢያንስ 32 ሰዎችን ህይወታቸዉ ሲያልፍ ከ700 በላይ ሰዎች ቆስለዋል፡፡

ይህንን መረጃ የገለጹት ተጠባባቂዋ ፕሬዚዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ ናቸው።

መንቀጥቀጦቹ 7.2 እና 7.5 መጠን ያላቸው ሲሆኑ፤ ከዋና ከተማዋ ካራካስ በስተምዕራብ በሚገኝ አካባቢ ተከስተዋል።

በካራካስ በፈራረሱ ሕንጻዎች ፍርስራሽ ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን ለማዳን ፍለጋዉ የቀጠለ ሲሆን፤ ከፍርስራሹ ውስጥ የእርዳታ ጥሪዎች እየተሰሙ መሆናቸው ተገልጿል።

አደጋው የተከሰተው በአገሪቱ ብሔራዊ በዓል ቀን ሲሆን፤ አብዛኞቹ ሰዎች በቤታቸው ውስጥ በነበሩበት ሰዓት ነው።

የአሜሪካ ጂኦሎጂ ጥናት ተቋም ቀደም ሲል ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ሊሞቱ የሚችሉበት 44በመቶ ዕድል እንዳለ እና ከ1መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ሊሞቱ የሚችሉበት 30 በመቶ እድል እንዳለ ገምቶ ነበር።

ባለሥልጣናት የሟቾችና የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል በመግለጽ የማዳን ሥራው በቀጣይነት መቀጠሉን አስታውቀዋል።

ትዕግስት ግርማ

ሰኔ 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *