ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንዳሉት፤‹‹እስከ ሰኔ 20 ቀን 2026 ድረስ የክልሉ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 8መቶ38 የተጠረጠሩ የኮሌራ ተጠቂዎችን፣ 7 የተረጋገጡ ታካሚዎችን እና 1መቶ17 ሞቶችን ሪፖርት አድርጓል፡፡
ወረርሽኙ የተከሰተው ‹‹በግጭት ምክንያት የጤና አገልግሎቶች መቋረጥ››በሰፈነበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።
‹‹የህዝብ መፈናቀል መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ማግኘት ይበልጥ አስቸጋሪ እያደረገው ነው። በተመሳሳይ ጊዜ የጸጥታ ችግር እና የመንገድ ተደራሽነት ውስንነቶች የምላሽ ሰጪ ቡድኖችን ለማሰማራት እንዲሁም የሕክምና ቁሳቁሶችን እና ሰብአዊ ድጋፎችን ለማድረስ መዘግየትን እየፈጠሩ ነው››ብለዋል።
ዶክተር ቴዎድሮስ አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመሆን የኮሌራ ሕክምና መስጫ ማዕከላትን እና በአፍ የሚወሰድ የሰውነት ፈሳሽ መተኪያ ጣቢያዎችን በማስፋፋት፣ የኮሌራ መከላከያ ቁሳቁሶችን በማቅረብ፣ የእጅ መታጠቢያ ጣቢያዎችን በመገንባት፣ የጤና ባለሙያዎችን በማሰልጠን እንዲሁም የማህበረሰብ ጤና ትምህርትን በመደገፍ የጤና ምላሹን በማስተባበር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
እስከዳር ግርማ
ሰኔ 23/2018 ዓ.ም
