የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የአዕምሮ እና አካላዊ ህክምናን አጣምሮ የሚሰጥ ሆስፒታል ሲሆን፤ከየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ተብሏል፡፡
የሆስፒታሉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መገርሳ ዓለሙ፥በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በሰሜኑ ግጭት ወቅት በደረሰበት ጫና ምክንያት በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት በ85 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገለት እድሳት ተጠናቆ አሁን ላይ ወደ ስራ መግባቱን አመልክተዋል።
ተቋሙ በአሁኑ ወቅት የኦፕሬሽን ክፍሎቹን ከ5 ወደ 10 ያሳደገ ሲሆን፥የሱስ ተጠቃሚዎች ተኝተው የሚታከሙበት ማዕከል፣ ዘመናዊ የጭቅላ ህጻናት ህክምና እና አዲስ የማይክሮ ባዮሎጂ ላቦራቶሪ አደራጅቷል።
ሆስፒታሉ በሚቀጥሉት 5 እስከ 10 ዓመታት ውስጥ የአዕምሮ፣ የነርቭ እንዲሁም የአንጎል እና የነርቭ ቀዶ ህክምናን በማቀናጀት የኒውሮ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ለመሆን እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የሚታየውን የሰው ኃይል ውስንነት እና የህክምና ግብዓቶች ዋጋ መጨመርን ለመቋቋም አገልግሎቱን በእጥፍ የሚያሳድግ አዲስ ህንፃ ለመገንባት የዝግጅት ሂደቶች ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እንደደረሱም አመልክተዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ሰኔ 23/2018 ዓ.ም
