ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተነሡ ጥያቄዎች፦

በ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል፡

አነስተኛ ገቢ ላላቸው እና ለመንግሥት ሠራተኞች የኑሮ ጫናን ለመቋቋም ምን ታስቧል፤ ከሚመሠረተው አዲሱ መንግሥት ምን እንጠብቅ?

የሰላም የጸጥታ እና የፖለቲካ ውድቀት በግልጽ በባለፈው በጀት አመት ታይቷል ይሄንን ለማሻሻል ምን ምን ጉዳዮችን ለመስራት ታቅዷል?

የወደብ የኅልውናችን ጉዳይ ነው፤ የወደብና የባህር በር ጉዳይ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ቢገልጹልን?

የመንግሥት መዋቅር ተጠቅሞ በዜጎች ላይ ምዝበራ የሚፈጽሙ አካላት ላይ ገዥው ፓርቲ መዋቅሩን የማጽዳት እና ተጠያቂነትን የማስፈኑን ጉዳይ እንዴት ሊያስተካክለው አስቧል?

ከፀጥታ አኳያ እየተሻሻሉ ያሉ ጉዳይ ቢኖርም፣ አሁንም አንዳንድ ቦታዎች ችግሮች አሉ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን መፍትሔ ለመስጠት ታስቧል?

ከነዳጅ ጋር በተያያዘ፦ መንግሥት ለነዳጅ ድጎማ ቢያደርግም የነዳጅ ሽያጭ እና ስርጭት ከብልሹ አሠራር ሊድን አልቻለም። በዚህ ላይ መንግሥት የያዘው መፍትሔ ምንድን ነው?

መንግስት የተደበቀ እዳን በተመለከተ ያለውን ሁኔታ ለማሳየት ምን ያህል ግልጽነት ይታይበታል ?

የመንግስት የትምህርት ጥራት በተመለከተ የሰራቸው ስራዎቸ ምን ያህል ችግር ቀራፊ ነበሩ ይሄንን ድጋሚ ለመከለስ ምን ምን እቅዶች ተይዘዋል? የሚሉት ይገኙበታል

ከምክር ቤቱ አባላት እየቀረቡ ባሉ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

ለዓለም አሰፋ

ሰኔ 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *