ከ5 ወደ 7 ሚሊዮን፤ የ«ኢትዮጵያ ኮደሮች» መርሃ ግብር አዲስ ምዕራፍ

የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሆነው የኮደሮች ማሰልጠኛ መርሃ ግብር፣ በሁለት ዓመት ውስጥ 5 ሚሊዮን ወጣቶችን ለማሰልጠን አቅዶ የነበረውን ግብ ከተቀመጠለት ጊዜ ቀድሞ አሳክቷል።
 
እስከ ሰኔ 2026 ድረስ ከ5 ሚሊዮን በላይ (5,005,146) ሰልጣኞችን መመዝገብ የቻለው ይህ ፕሮጀክት፣ አሁን አድማሱን በማስፋት ተጨማሪ 2 ሚሊዮን ወጣቶችን ለማሳተፍ መታቀዱን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኤምባሲ ለጣያችን በላከው መግለጫ ገልጻል፡፡
 
ይህ ስኬት የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ጉዞ የሚያፋጥን መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ለኤምሬትስ መንግስት ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
 
የኤምሬትስ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር መሐመድ አብዱላህ አል ገርጋዊም ፕሮግራሙ ወጣቶችን ለነገው የሥራ ዓለም ብቁ እንደሚያደርጋቸው አረጋግጠዋል።
 
መርሃ ግብሩ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ደረጃ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግሩን ለመደገፍ አልሞ እየሰራ ይገኛል።
 
ሐምሌ 02/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *