አይ ኤም ኤፍ በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ምክንያት የዓለም የኢኮኖሚ ዕድገት ግምቱን ቀነሰ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የዘንድሮውን የዓለም የኢኮኖሚ ዕድገት ግምት በ2025 ከነበረበት 3.5 በመቶ ወደ 3 በመቶ ዝቅ አድርጎታል።

ድርጅቱ ባወጣው የቅርብ ጊዜ የዓለም የኢኮኖሚ ዕይታ ሪፖርቱ፤ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት፣ የኢነርጂ ዋጋ መናር እና ቀጣይነት ያለው የጂኦፖለቲካዊ አለመረጋጋት በዓለም አቀፍ የምርት ዕድገት ላይ ጫና ማሳደራቸውን እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቋል።

ሆኖም ግን በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ላይ እየተደረገ ያለው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ከግጭቱ የሚመጣውን አሉታዊ ተፅዕኖ በከፊል እያካካሰው መሆኑን አይ ኤም ኤፍ ገልጿል።

በሸቀጦች ዋጋ መናር ምክንያት፤ የዓለም የዋጋ ግሽበት ባለፈው ዓመት ከነበረበት 4.1 በመቶ በ2026 ወደ 4.7 በመቶ ከፍ ይላል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንም እንኳን ትንበያው ደካማ ቢሆንም፣ የዓለም ኢኮኖሚ የመቋቋም አቅም ማሳየቱን እና በ2027 ዕድገቱ ወደ 3.4 በመቶ ያገግማል ተብሎ እንደሚጠበቅ አይ ኤም ኤፍ አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ስጋቶች አሁንም ከፍተኛ መሆናቸውን ያስጠነቀቀው ድርጅቱ፤ማንኛውም አዲስ የኢነርጂ አቅርቦት መስተጓጎል ወይም የጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች መባባስ የዓለምን ኢኮኖሚ የበለጠ ሊያዳክመው እንደሚችል ገልጿል።

እስከዳር ግርማ

ሐምሌ 02/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *