የኻሚኒ አስከሬን ከማረፉ በፊት መሽሃድ ከተማ ገባ

የቀድሞው የኢራን የበላይ መሪ አሊ ኻሚኒ አስከሬን የያዘችው አውሮፕላን የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከመፈጸሙ በፊት በምስራቃዊቷ የተቀደሰች ከተማ መሽሃድ አርፋለች።
 
የሀገሪቱ  የዜና ወኪል ኢርና (IRNA)፣ የማሃን ኤር አውሮፕላን  በኻሚኒ የትውልድ ከተማ አየር ማረፊያ ካረፈ በኋላ በዝግታ ሲጓዝ የሚያሳይ ምስል አስተላልፏል።
 
አስከሬኑ የተጓጓዘው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት በተቀደሱት የነጃፍ እና የከርባላ ከተሞች የክብር ሥነ ሥርዓት ከተከናወነበት ከኢራቅ ነው።
 
ዛሬ በኢራን እንዲሁም በጎረቤት ሀገር ኢራቅ ውስጥ ለአምስት ቀናት በአምስት ከተሞች የተካሄደውና በተቀናጀ ሁኔታ የተመራው የሕዝባዊ ሐዘን መግለጫ ሥነ ሥርዓት የመጨረሻ ቀን ነው።
 
ይህም የኢራን አዲስ መሪዎች አንድነትንና ጥንካሬን ለማሳየት እንዲሁም በዚህ ጦርነት የመጀመሪያዎቹ ሰዓታት ላይ የተገደሉት የበላይ መሪያቸው ለኢራን ብቻ ሳይሆን ለሰፊው የሺዓ ሙስሊም ማኅበረሰብ ጭምር ትልቅ ቦታ ያላቸው መሆኑን ለማስመር ያደረጉት ጥረት ነበር ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
 
ሐምሌ 02/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *