የማርና የዓሳ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩና የመኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች መስፋፋታቸው ተገለጸ

በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የማር ምርትን 428 ሺህ ቶን ማድረስ መቻሉን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ እንደገለጹት፣ የማር ምርት በባህላዊ ቀፎ በዓመት 10 ኪሎ ግራም ምርት ብቻ የነበረ ሲሆን አሁን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በተሰራው ስራ፣ የሀገሪቱ ዓመታዊ የማር ምርት 428 ሺህ ቶን ደርሷል።

የዘመናዊ ቀፎዎች ስርጭት መጨመርና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለንቦች ምግብ መገኘት አስተዋጽኦ ማድረጉን ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ገልጸዋል። በዓሳ ምርት በኩልም የጫጩት ስርጭት ከ300 ሺህ ወደ 16.5 ሚሊዮን በማደጉ፣ ምርቱ ከ78 ሺህ ቶን ወደ 207 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል ብለዋል።

ለነዚህ ውጤቶች መገኘት እንደ ዋነኛ ደጋፊ የተጠቀሰው የመኖ አቅርቦት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ 228 የተቀነባበረ መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በይፋ ተመዝግበው ስራ መጀመራቸው ተጠቁሟል።

በተለይም እንደ ጅግጅጋ ባሉ አካባቢዎች በቀን 120 ሺህ ቶን የሚያመርቱ ግዙፍ ፋብሪካዎች መገንባታቸው ለዘርፉ እድገት ትልቅ አቅም መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ዛሬ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል።

አዲስዓም አበበ

ሐምሌ 02/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *