ባማኮን ሪልስቴት ያስገነባቸውን አፓርታማዎች ለባለቤቶቻቸው አስረከበ

ባማኮንሪልስቴት በቦሌ ያስገነባቸውን ዘመናዊ አፓርታማዎች ለባለቤቶቻቸው አስረክቧል።

በግንባታው ዘርፍ ከ20 ዓመታት በላይ ተሻግሯል የተባለው ኩባንያው ያስረከባቸው እነዚህ አፓርታማዎች ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፊት ለፊት የሚገኙ ሲሆን፥በተለይም ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ተጓዦች ተመራጭ መኖሪያዎች ናቸው ተብሏል።

ቤቶቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ከመቅረባቸውም በላይ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ በመሆናቸው ባለቤቶቹ በራሳቸው መኖር አሊያም በቀጥታ አከራይተው ከፍተኛ ገቢ ማግኘት የሚችሉባቸው እንደሆኑ ተጠቅሷል።
ባማኮን ሪልስቴት ግንባታዎቹን በታቀደላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በራሱ በባማኮን ግሩፕ ሥር ካሉ እህት ኩባንያዎች ጋር በጥምረት እንደሚሰራ ገልጿል።

ከዚ ቀደም በካዛንችስ ፣ ባምቢስ አትላስ፣ፍሬንድሺፕ ፓርክ፣ቦሌ ኤርፖርት ቪው ፣በሜክሲኮ እና ቡልቡላ ሳይቶች ላይ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ግንባታዎችን አጠናቆ ለደንበኞች ማስረከቡ ተገልጿል።

ሀና ሰይፉ

ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *