ኮርፖሬሽኑ በ2018 በጀት ዓመት 2መቶ66.9 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን አስታዉቋል
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች ተመርተው ወደ ውጭ አገራት ከተላኩ ምርቶች በ2018 በጀት ዓመት 2መቶ66.9 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ እንደገለጹት፤በበጀት ዓመቱ የተገኘው የውጭ ምንዛሬ ገቢ ተቋሙ ከተቋቋመ ወዲህ የተመዘገበው ከፍተኛው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን በሀዋሳ ከተማ በመገምገም ላይ ይገኛል።
ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም
