ኢራን የህልውና ጦርነት መጀመሩን አስታወቀች

በአሜሪካ ጥቃት ምክንያት የሰላም ስምምነቱ መፍረሱንና «የህልውና ጦርነት» መጀመሩን ኢራን አስታወቀች

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ሰኔ 17 ቀን ተደርሶ የነበረው ጊዜያዊ የሰላም ስምምነት፤ አሜሪካ በኢራን የወደብ ከተሞችና ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃትና የባህር ከበባ ማድረጓን ተከትሎ ሙሉ በሙሉ ፈርሷል።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በባንዳር አባስ፣ ቻባሃር እና አህቫዝ በሚገኙ የኢራን የዕዝ ማዕከላት፣ የጸረ-አውሮፕላን መከላከያዎች እና የሚሳዔል ጣቢያዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽሟል።

በጥቃቱ ቢያንስ 35 ሰዎች ሲገደሉ ከ3መቶ በላይ መቁሰላቸውን የኢራን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተጨማሪም የአሜሪካ ጦር በኢራን ወደቦች ላይ ዕገዳ የጣለ ሲሆ፤ አንድ የነዳጅ ጫኝ መርከብ በሚሳዔል መምታቱን ገልጿል።

የኢራን ከፍተኛ ተደራዳሪ መሀመድ ባገር ቃሊባፍ ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር «የህልውና ጦርነት» ውስጥ መሆኗን ገልጸው፤ የሀገሪቱ ጦር ኃይል አሁን ላይ ሙሉ የዕርምጃ ነጻነት እንዳለው አውጀዋል።

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም አሜሪካ ቃልኪዳኗን በማፍረሷ ምክንያት ኢራን ከስምምነቱ መውጣቷንና ለጊዜውም ምንም ዓይነት አዲስ ድርድር እንደማታደርግ አስታውቋል።

በአጸፋው የኢራን እስላማዊ አብዮት ጥበቃ ኃይል በባህሬን የሚገኘውን የአሜሪካ አምስተኛ የባህር ኃይል ዕዝ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ክልላዊ የጦርነት ዕርምጃዎችን መጀመሩን አስታውቋል።

ሳራ ዮሐንስ

ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *