ስድስት ሚሊየን የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ በአመቱ ተከናውኗል – የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

አገልግሎቱ ከፓስፖርት፣ ቪዛ፣ ትዉልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አየር ድንብር እና የየብስ ድንበር አስተዳደርን የበጀት አመት አፈፃፀም ክንውኖችን በተመለከተ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2018 ዓ/ም በጀት አመት የእቅድ አፈጻጸም ካለፉት አመታት አንፃር የተሻለ መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፥በበጀት አመቱ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች መሰጠት መቻሉን አንስተዋል፡፡

ከቪዛ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በበጀት አመቱ 1,046,286 ቪዛ ተሰጥቷል፣ ለ32ሺህ9መቶ52 ትውልደ ኢትዮጵያውያን መታወቂያ እንዲሁም ለ21ሺህ 1መቶ63 ነዋሪዎች ጊዜያዊና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ መሰጠቱን በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።

በአጠቃላይ ከ42 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ የተገለፀ ሲሆን፥በአየር እና በየብስ ድንበር አለምዓቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ በጉዞ ሰነድ ለ7,225,691 ገቢና ወጪ መንገደኞች አገልግሎት ተሰጥቷል።

በበጀት አመቱ ስድስት ሚሊየን የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ የተመዘገበ ሲሆን ፥ይህን ሂደት ለመምራት የተለዩ የዲጂታል አማራጭ መተግበሪያ እና ስርዓት መዘርጋቱን ዋና ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።

ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *