ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለ10 ቀናት የሚቆይ የህክምና አገልግሎት አዘጋጀየቀዶ ሕክምና፣ የዓይን፣ የጥርስ፣ የቆዳ እና የአዕምሮ ሕክምና አገልግሎቶች በሆስፒታሉ በነፃ መሰጠት ጀምሯል።

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 30 ሚልየን ብር የሚገመት የህክምና  አገልግሎትን ለ200 ሺህ ዜጎች በነጻ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ረድኤት ሰለሞን እንደገለጹት፥ፕሮግራሙ በየካ ክፍለ ከተማ ግቢ ውስጥ በትናንትናዉ ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

ከዚህም በተጨማሪ የሕጻናት፣ የማኅፀንና ፅንስ ሕክምናዎችን ጨምሮ ከአንገት በላይ ሕክምናዎችም መካተታቸዉንና ለሕክምናው የሚያስፈልጉ መድኃኒቶች እና የላብራቶሪ ምርመራዎች በነጻ እንደሚቀርቡም ገልጿል።

ተጨማሪ ክትትል የሚያስፈልጋቸው ወይም ከተቋሙ አቅም በላይ የሆኑ ታካሚዎች ወደ ተመረጡ የሕክምና ተቋማት በሪፈር ይላካሉ ተብሏል።

ሆስፒታሉ  የበጎ ፍቃድ ስራዉን ለሦስተኛ ዓመት እያከናወነው እንደሆነ በመግለፅ ባለፈው  ዓመት ለ1መቶ95 ሺህ ሰዎች የነጻ ሕክምና አገልግሎት መስጠቱን  አስታውሷል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *