በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 6 ዙር በረራ 1ሺህ 4መቶ 81 ኢትዮጵያዊያን መመለሳቸዉን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋ፡፡
የተመለሱት 8መቶ79 ወንዶች፣ 5መቶ54 ሴቶች እና 48 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ፤ከተመላሾች መካከል 82 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ87 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል ተብሏል።
ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡
በተጨማሪም መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደ ተለያዩ ሀገራት ሄደው የሚመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ ተግባራትን በትብብር እያከናወነ መሆኑን ገልጿል፡፡
ወደፊትም በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማበረታታት ሚኒስቴሩ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግሯል፡፡
ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም
