በ24 ሺህ ብር የተነሳው ‘ተደራሽ’ የቁጠባና ብድር ማህበር ካፒታሉን 1.24 ቢሊየን ብር ማድረሱን አስታወቀ

በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማህበራት የዜጎችን የቁጠባ ባህል በማዳበር እና የፋይናንስ ፍላጎትን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ከፍተኛና ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም ሰምተናል ።

ይህ የተባለው “ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር” 9ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች ባከበረበት ወቅት ነው።

በበዓሉ አከባበር ስነ-ስርዓት ላይ የማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ታመነ እንደገለጹት፤ ማህበሩ ባለፉት ዓመታት የካፒታል አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችሏል።

በዚህም አጠቃላይ ለአባላቱ ያሰራጨው የብድር መጠን ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን ዋና ስራ አስኪያጁ ይፋ አድርገዋል።

ማህበሩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያሳየውን ሁለንተናዊ እድገት በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት አቶ አለማየሁ፤ በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ የቅርንጫፎቹን ቁጥር 33 ማድረስ መቻሉንና የደንበኛ አባላቱም ቁጥር ከ27 ሺ በላይመሻገሩን አስታውቀዋል።

ይህ የቅርንጫፎችና የአባላት ቁጥር መጨመር ማህበሩ የፋይናንስ ፍላጎትን ተደራሽ ለማድረግ እያደረገ ያለውን ጉዞ የሚያሳይ መሆኑም በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ለዓለም አሰፋ

ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *