ባለፈው ወር በደረሰው አደጋ 16 ሺህ7መቶ40 ሰዎች መቁሰላቸውን የብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ገልጸዋል።
ባለፈው ወር በቬኔዙዌላ በተከሰቱት ተከታታይ የመሬት መንቀጥቀጦች የሟቾች ቁጥር 5 ሺህ3መቶ46 መድረሱን ተገልጿል።
ባለስልጣናት ለ1መቶ28 ሺህ3መቶ24 ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረጋቸውን እና 21 ሺህ2መቶ35 ሰዎችን የሚይዙ 1መቶ7 ጊዜያዊ መጠለያ ካምፖችን ማቋቋማቸውን የገለጹ ሲሆን፣ 17 ሺህ9መቶ7 ሰዎች ደግሞ አሁንም ቋሚ መኖሪያ ቤት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ 8መቶ56 ህንፃዎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 1መቶ90ዎቹ ሙሉ በሙሉ ፈርሰዋል።
በሬክተር ስኬል 7.2 እና 7.5 የተመዘገቡት ሁለቱ የመሬት መንቀጥቀጦች፣ የደቡብ አሜሪካዊቷን ሀገር የመቷት ሰኔ 24 ነበር።
እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም
