ጥቃቱ የተፈጸመው ለቀናት የዘለቀውን ተቃውሞ ተከትሎ አዲስ የጦር አዛዥ ከተሾመ በኋላ ነው።
የዩክሬን ሰው አልባ ሲስተምስ ጦር አዛዥ ሮበርት ብሮቭዲ እንደተናገሩት፥የዩክሬን ድሮኖች ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ በጥቁር ባህር እና በአዞቭ ባህር ላይ 13 የሩሲያ መርከቦችን መምታታቸውን ገልጸዋል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በኦዴሳ ክልል በሚገኙ የዩክሬን ወደቦች እና ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል።
ሞስኮ በጥቃቱ ምክንያት ሁለት የባህር ኃይል መርከቦች እንዲሁም ወታደራዊ ጭነቶችን ለማውረድ እና ለማከማቸት የሚያገለግሉ የወደብ መሰረተ ልማቶች፣ የነዳጅ እና ቅባት ማከማቻ ታንኮች መመታታቸውን ተናግራለች።
ቅዳሜ ዕለት በዩክሬን ድሮኖች የተፈጸመው የቀድሞ ጥቃት ስምንት ሠራተኞችን የገደለ፣ የእሳት አደጋ ያስከተለ እና የዋይልድቤሪስን ሥራዎች ያስተጓጎለ ነበር ሲል ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል።
ሳራ ዮሐንስ
ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም
