የትራምፕ አስተዳደር ከሳዑዲ ዐረቢያ ጋር የደረሰው የኒውክሌር ስምምነት ከመካከለኛ ምስራቅ ጋር የነበረውን የዓመታት አቋም የቀየረ ሆኗል፡፡
የቀደሙት የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ሳዑዲ ዐረቢያ ለሲቪል የኃይል ማመንጫ ፕሮግራሞች የሚሆን የአሜሪካን የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ለማግኘት ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ማስተካከል አለባት በሚለው አቋም ላይ ይጸኑ ነበር፡፡
ከነዚህ መሪዎች በተቃራኒ ግን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነቱ በስፍራው የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ሽሚያ ሊቀሰቅስ ይችላል በሚል ከተሰነዘሩ ተቃውሞዎች ባሻገር፣ ለእስራኤል ምንም ዓይነት የፖለቲካ ጥቅም ሳይጠይቁ ለሳዑዲ ዐረቢያ የፈለገችውን ሰጥተዋታል፡፡
ይህ ስምምነት ትራምፕ እስራኤልን ማዕከል ያደረገውን እና ለእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት የሁለት ሀገራት መፍትሔ የመፈለግ ልማዳዊ የአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ አካሄድን ውድቅ ማድረጋቸውን የሚያሳይ የቅርብ ጊዜ ማሳያ ነው፡፡
ትራምፕ በሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው ከቻይና እና ከሌሎች ተፎካካሪዎች ጋር ለመወዳደር የአሜሪካን ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ በማጠናከር ላይ ትኩረት አድርገዋል፡፡
ተነታኞች እንደሚያስረዱት ከሳዑዲ ዐረቢያ ጋር የተደረገው የኒውክሌር ስምምነት አሜሪካ እስራኤልን ብታስቀይም እንኳ ቀጣናዊ ወዳጆቿን በጉያዋ አጥብቃ መያዝ እንደምትፈልግ መልዕክት ያስተላለፈ ነዉ፡፡
«በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ሀገራት የኒውክሌር መሰረተ ልማታቸውን ማልማት ይፈልጋሉ፤ አሜሪካ ባትሳተፍበት እንኳ ይህን ማድረጋቸው አይቀርም ዋሽንግተን ደግሞ አሁን ላይ ይህን እውነታ እየተቀበለች ይገኛል» ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ጥቅምን መሠረት ያደረገ የውጭ ሀገር ፖሊሲ የትራምፕ ሁለተኛው የሥልጣን ዘመን መለያ ሆኗል፡፡
ሀና ሰይፉ
ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም
