የኢራን ጦር ከቀድሞው ጊዜ በተሻለ ሁኔታ መዘጋጀቱን ቃል አቀባዩ ገለጹ

የኢራን ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል አሚር መሀመድ ኢራን ወታደራዊ ኃይሎች ከቀድሞው ጊዜ በበለጠ የዝግጅት አቅም ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

ለኢራን የመከላከያ ፕሬስ የዜና ወኪል በሰጡት ቃለ ምልልስ፤በተኩስ ማቆም ወቅት የተገኘውን ዕድል በመጠቀም የውጊያ ዝግጅታቸውንና የመዋጋት አቅማቸውን ማጠናከራቸውን ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ እንዳሉት፤ የኢራን ጦር ለማንኛውም ሊፈጠር ለሚችል ሁኔታ ዝግጅቱን አሻሽሎ እንደሚገኝ ገልጸው፣ በጠላት ሊወሰድ የሚችለውን ማንኛውንም እርምጃ ቀላል በማድረግ እንደማይመለከቱት አስታውቀዋል።

አክለውም ጠላት በመሬት ኃይል ወረራ ቢፈጽም ከአየር ወይም ከሚሳኤል ጥቃቶች የበለጠ ተጋላጭ እንደሚሆን ገልጸው፤የመሬት ውጊያዎች በተቃዋሚው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሰፊ እድል እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

የኢራን ጦር በመሬት ላይ በሚደረጉ ወታደራዊ ዘመቻዎች ውጤታማነቱና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅሙ ከፍተኛ እንደሚሆን አስረድተዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ትዕግስት ግርማ

ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *