ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኡመን ሀይር እንደገለጹት፥ከተያዘው እቅድ ውስጥ 40 ሺህ ዩኒት ደም በአዲስ አበባ፣ ቀሪው 1መቶ10 ሺህ ዩኒት ደም ደግሞ በክልሎች ደረጃ የሚሰበሰብ ይሆናል።
ባለፈው ዓመት የክረምት ወቅት 1መቶ40 ሺህ ዩኒት ደም መሰብሰቡን ያስታወሱት ወ/ሮ ኡመን፤ ዘንድሮ የተያዘው እቅድ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ10 ሺህ ዩኒት ጭማሪ እንዳለው አስገንዝበዋል።
ልዩ የክረምት የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ ንቅናቄው ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፥ እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥልም ስራ አስፈፃሚዋ ጠቁመዋል።
ሳራ ዮሐንስ
ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም
