የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ስራዎች ይፋ አድርጓል፡፡
በበጀት አመቱ ከ6መቶ 43 ሺህ 8መቶ25 ዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ መስጠት ተችሏል ተብሏል
ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ዮሴፍ ንጉሴ እንደገለፁት፤1መቶ96 ሺህ 1መቶ32 ያላገባ አገልግሎት ለመስጠት የተቻለ ሲሆን፤ ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር በ22 በመቶ ብልጫ እንደሚያሳይ አንስተዋል።
ኤጀንሲው በየወረዳው የሚገኙ በሚሊየን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን የወረቀት መዛግብትንና ማህደርን በስካኒንግ ማሽን ወደ ዲጂታል ሰነድ ማስተዳደሪያ ሥርዓት የመቀየር ተግባራት አከናዉኗል።
ኤጀንሲው የገፅ ለገፅ ግንኙነትን በማስቀረት ነዋሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበትን መተግበሪያ በማዘጋጀት በዚህ መተግበሪያ አማካኝነት ኦንላይን የልደት ካርድ፣ የነዋሪነት መታወቂያ፣ያላገባ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ 1 ሚሊየን 8መቶ 28 ሺህ 8መቶ 46 ዜጎችን መመዝገብ የተቻለ ሲሆን፤ እስካሁን ድረስ 8 ሚሊየን ዜጎችን በፋይዳ መታወቂያ ለመመዝገብ ተችሏል፡፡
ተቋሙ ብልሹ ተግባራትን እና አደጋዎች በማጋለጥ ተጠያቂነት ለማስፈን የተወሰደ ተጨባጭ እርምጃዎችን በተመለከተ በበጀት ዓመቱ ውስጥ 13 አመራር፣ 78 ፈጻሚ እና 14 ባለጉዳይ በድምሩ 1መቶ5 ሰዎችን ተጠያቂ መደረጉ ተገልጿል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም
