አቢሲንያ ባንክ በኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕል ንዋዮች ገበያ (ESX) ዋና መድረክ ላይ በይፋ መመዝገቡን አስታወቀ

የባንኩ መመዝገብ በኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕል ንዋዮች ገበያ የግብይት መድረክ በተካሄደ የደወል መደወል ሥነ-ሥርዓት የተከበረ ሲሆን፤ በሁነቱ ላይ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የአቢሲንያ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድና ከፍተኛ አመራሮች፣ የገበያ ተሳታፊዎች፣ ኢንቨስተሮችና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕል ንዋዮች ገበያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል፤ባደረጉት ንግግር የባንኩን ገበያውን የተቀላቀለበትን ሁኔታና የሂደቱን ጠቃሚነት አብራርተዋል።

ዶ/ር ጥላሁን በንግግራቸው እንደገለጹት፤ በገበያው ላይ የሚደረግ እያንዳንዱ አዲስ ምዝገባ የሰነደ መዋዕል ንዋዮችን መሠረት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል።

አክለውም የአቢሲንያ ባንክ በገበያው ላይ በይፋ ለመመዝገብ ያደረገው ውሳኔ በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ላይ በተቋማት ዘንድ እየጨመረ የመጣውን እምነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህም የኢትዮጵያ መሪ ኩባንያዎች ከፍተኛ የተቋማዊ አስተዳደር፣ ግልጽነት እና የኢንቨስተሮች ተሳትፎ መርሆዎችን እየተቀበሉ መሆናቸውን እንደሚያመላክት ገልጸዋል።

ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ከኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ጋር አብሮ ያደገው አቢሲንያ ባንክ በገበያው በይፋ መመዝገቡ በበለጠ ግልጽነት፣ በተሻለ ተቋማዊ አስተዳደር፣ለባለሃብቶች ባለው ከፍተኛ ተጠያቂነትና ከኢንቨስተሮች ጋር በሰፊው ተሳትፎ ወደሚያደርግበት አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሽጋግረዉም ተገልጿል።

ለዓለም አሰፋ

ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *