የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ በወረዳ ደረጃ መታተም ተጀመረ

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ በወረዳ ደረጃ በመታተም ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው የህብረተሰቡን የአገልግሎት ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ሲሆን የከተማዋን ነዋሪዎች እንግልት ለመቀነስ በማዕከል እና በክፍለ ከተማ ደረጃ በመታተም ሲሰራጭ የነበረውን የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ በወረዳ ደረጃ በማተም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በመጀመሪያ ዙር ከፍተኛ ተገልጋይ ባላቸው 22 የተመረጡ ወረዳዎች የተጀመረው ይህ አገልግሎት፤ደንበኞች ጥያቄያቸውን ባቀረቡበት ቅጽበት መታወቂያቸው ታትሞ ወዲያውኑ እንደሚሰጣቸው የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ገልጸዋል።

በቀጣይም በቀሪ ወረዳዎች ላይ የመታወቂያ ህትመት ተግባራዊ እንደሚደረግ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው የነዋሪዎችን እንግልት በመቀነስ ፈጣን ፣ቀልጣፋ እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት ነዋሪዎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት የሚጠይቁበት እና የሚስተናገዱበት የኦን ላይን አገልግሎት ወደ ስራ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡

ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *