በግብፅ የሀሰት ዳኞችን በመስሰል ሰዎች ላይ ማጭበርበር የፈጸሙ ግለሰቦች ተያዙ

በግብፅ የሀሰት ዳኞችን በመምሰል በሰዎች ላይ የማጭበርበር ሴራ ፈጽመዋል የተባሉ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
 
የግብፅ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ ማጭበርበሩ በሐሰተኛ የችሎት ትዕይንቶች እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እውነተኛ ዳኛ በመምሰል የተፈጸመ ነው።
 
ዋና ተጠርጣሪዎቹ በካይሮ እና በጊዛ የሚኖሩ ሥራ አጥ ግለሰብ እና ተማሪ ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር ውለው እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
 
በምርመራ ወቅትም ከሕዝብ ገንዘብ ለመውሰድ የሚያስችል የወንጀል ቡድን ማቋቋማቸውን አምነዋል። ገንዘቡን የወሰዱትም ከመንግስት መስሪያ ቤቶች የቤት እድል እንደሚያመቻቹ በሐሰት ቃል በመግባት እንደሆነ ተናግረዋል።
 
በተጨማሪም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመተባበር የሐሰት ችሎት ትዕይንቶችን ማዘጋጀታቸውን ማመናቸው ተነግሯል።
 
መንግስታዊው የአል-አህራም ጋዜጣ እንደዘገበው በሴራው ተሳታፊ ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው አስቸኳይ የወንጀል ፍርድ ሂደት እንዲጀመርባቸው ተደርጓል።
 
ይህ የማጭበርበር ሴራ ይፋ የሆነው፣ አንድ ግለሰብ ራሱን ዳኛ አድርጎ ባቀረበ ሰው መታለሉን ለባለስልጣናት አቤቱታ አቅርቦ ምርመራ ከተጀመረ በኋላ ነው።
 
ከዚያም ዋናው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ ፖሊስም የጦር መሳሪያ፣ የዳኝነት መታወቂያ እና የሐሰት የዳኝነት ማዕረጉን የሚያሳዩ መታወቂያዎችን መያዙን ጋዜጣው አክሎ ገልጿል።
 
ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *