ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ወሳኙን የሆርሙዝ ወሽመጥ የባህር መስመር ለማስከፈት ከኢራን ጋር ስምምነት ይደረጋል የሚል ተስፋ መስጠታቸዉን ተከትሎ፣ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የፋይናንስ ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት እንደተናገሩት፤የነዳጅ ጭነቶች ምናልባት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሊቀጥሉ የሚችሉበት እድል ይኖራል፡፡
እጥረቱ ሊቀረፍ ይችላል በሚለው ዜና ምክንያት የአለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መለኪያ የሆነው የብሬንት ክሩድ ዋጋ 5በመቶ ያህል በመቀነስ ከአንድ በርሜል ከ80 ዶላር በታች ወርዷል።
ነገር ግን በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል ያለውን ግጭት ለማርገብ ባለፉት ወራት የተደረጉ ውይይቶች አለመሳካታቸው፣ በነዳጅ ገበያው ላይ መዋዠቅ ያስከተለ ሲሆን፤ ይህም በየማደያው የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ አሽከርካሪዎችን ጎድቷል።
ሀና ሰይፉ
ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም
