ኤክስፐርት ትሬኒንግ ኢንስቲትዩት የኢ-ለርኒንግ ድረ-ገፅ እና የሞባይል መተግበሪያውን ይፋ አደረገ

ኤክስፐርት ትሬኒንግ ኢንስቲትዩት ኃ.የተ.የግ.ማ የሥልጠና አገልግሎቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ያበለጸጋቸውን «ኤክስፐርት» የተሰኘ የኢ-ለርኒንግ ድረ-ገጽ እና «ማይ ኤክስፐርት» የሞባይል መተግበሪያ አስመርቋል።

ይፋ የተደረጉት አዲሶቹ የዲጂታል አማራጮች ተማሪዎችና ባለሙያዎች የትምህርትና የሥልጠና ይዘቶችን በማንኛውም ጊዜና ቦታ ማግኘት እንዲችሉ የታለሙ ናቸው ተብሏል።

ይህም ሰልጣኞች በራሳቸው ጊዜና ፍጥነት እየተማሩ የሙያ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ እንዲሁም ከዘመናዊው የፋይናንስና የቴክኖሎጂ እድገት ጋር እንዲራመዱ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

በዕለቱ በተካሄደው መርሃ-ግብር ላይ የተቋሙ የብራንድ አምባሳደር ሹመትና የስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓትም አብሮ ተካሂዷል።

በዚህም መሠረት ተቋሙ የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀይለዓብ አመሀ ጋር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነት ተፈራርሟል።

ኤክስፐርት ትሬኒንግ ኢንስቲትዩት በፋይናንስና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ያተኮረ የሥልጠና ተቋም ሲሆን፤ በተለይም በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ፣ በብሎክቼን፣ በሳይበር ሴኪዩሪቲ፣ በፊንቴክ እና በሌሎች ዘመናዊ የፋይናንስ መስኮች ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞችን በአካልና በኦንላይን ሲሰጥ የቆየ ተቋም መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሐመረ ፍሬዉ

ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *