ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ለሰብዓዊ ድጋፍ ሥራው የሚያገለግል መሬት አገኘ

ከ25 ዓመታት በላይ ለችግረኛ ህጻናትና እናቶች የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎችን ሲያደርግ የቆየው ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር፣ ለሥራው የሚያገለግል መሬት ማግኘቱን ገልጿል።

ማህበሩ የበጎ አድራጎት ስራውን ለመደገፍ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለት የቦታ ድጋፍ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አንድ የቦታ ድጋፍ ማግኘቱን አስታውቁዋል

ማህበሩ በተለያዩ የሥራ ዘመናት ከ1 ሺህ 500 በላይ ህጻናትና እናቶችን በተለያየ መልኩ መደገፉን አንስቷል።

የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራውን በተለያዩ ቦታዎች ሲያከናውን የቆየው ማህበሩ፣ ቋሚ የሥራ ቦታ ማግኘት ከዋና ተግዳሮቶቹ አንዱ እንደነበር ጠቁሟል።

ማህበሩ ከዚህ በፊት ያቀረበው የመሬት ድጋፍ ጥያቄ ተመልሶ አሁን ቋሚ የሥራ ቦታ ማግኘቱ ለሥራው ቀጣይነት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ማህበሩ ገልጿል ።

ቋሚ ቦታ መገኘቱ ማህበሩ ለህጻናትና እናቶች የሚሰጣቸውን የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎቶች በተደራጀና ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲያከናውን እንደሚያግዘው ማህበሩ አስታውቋል።

በመጨረሻም ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ያገኘውን መሬት በመጠቀም ለችግረኛ ህጻናትና እናቶች የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ በተሻለ ሁኔታ ለማስቀጠልና ለማስፋፋት እንደሚሠራ አስረድቷል።

ሰላማዊት ዲታ

ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *