የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ተመካካሪዎች መግባባት ላይ ደረሱ ተባለ

የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦቻቸው መግባባት ላይ ደርሰዋል ሲል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡

5 መቶ አባላት ባሏቸው ስምንት የስራ ቡድኖች አጀንዳዎቹ ምክክር እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ያነሳው ኮሚሽኑ በአሰራሩ መሰረት 5 መቶ አባላት ያሉት አንድ ቡድን በአንድ አጀንዳ ላይ እየተመካካረ እንደሆነ አስታውሷል፡፡

በዚህም በሃይማኖት ጉዳዮች እና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሲመካካሩ የቆዩት ሁለት ቡድኖች ዛሬ ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም በተጠናቀሩ ምክረ ሃሳቦቻቸው ላይ ተስማማተው በተዘጋጀው ቃለ ጉባኤ ላይ ተፈራርመዋል ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ “የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦቻቸው መግባባት ላይ ደርሰዋል” ቢልም መግባባት ተደረሰባቸው ያላቸውን የሃይማኖት ጉዳዮች እና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ዝርዝር አልገለጸም፡፡

አዲስዓለም አበበ

ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *