የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤስፐን ባርት ኢዴ በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሻቅ ዳር ጋር የተወያዩ ሲሆን፥ይህም ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረገው ከፍተኛው የዲፕሎማሲ ጉብኝት ነው።
በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ግንኙነቶች፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በሰፊው የመከሩ ሲሆን፥ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓኪስታን በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ እና ጦርነቱን ለማስቆም የምታደርገውን የሰላም ማስታረቅ ጥረት ለዓለም ትልቅ ውለታ ሲሉ አድንቀዋል።
በተጨማሪም በኖርዌይ የሚኖሩ 60 ሺህ የሚጠጉ የፓኪስታን ተወላጆች ለሀገሪቱ ዕድገት እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
ሳራ ዮሐንስ
ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም
