ሞሮኮ የድንበር ላይ ጥበቃዋን ማጥበቋን ተከትሎ ተቃዋሚዎች በተሰበሰቡባት በሰሜን አፍሪካ የስፔን ግዛት ሴውታ ውጥረት ነግሷል፡፡
ተቃውሞው የተነሳው በማህበራዊ ሚዲያ ወደ ሴውታ በብዛት ለመሻገር የቀረቡ አዳዲስ ጥሪዎችን ተከትሎ ሲሆን፥ይህም ሌላ የፍልሰት ማዕበል እንዳይከሰት ስጋት ፈጥሯል።
ድንበሩ እንደተዘጋ ባለበት ሁኔታ ተቃዋሚዎቹ ‹‹ስፔን ለዘላለም ትኑር›› እና ‹‹ጥገኝነት›› የሚሉ ጽሁፎችን ሲያውለበልቡ ታይተዋል።
የስፔን መከላከያ ሚኒስትር ማርጋሪታ ሮብልስ፤ ወደ ግዛቱ በጅምላ ለመግባት የሚደረግ ማንኛውም አዲስ ሙከራ እንዳይኖር አስጠንቅቀዋል።
ይህ ማስጠንቀቂያ የመጣው በሐምሌ ወር መጨረሻ በድንበር ላይ በተከሰተ ግርግር ቢያንስ 80 ሰዎች መሞታቸው በይፋ ከተገለጸ በኋላ ነው።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል ይናገራሉ።
በመቀጠልም በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ወደ 72 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች በድንገት መግባታቸው ሰብዓዊ ቀውስ ያስከተለ ሲሆን፥ በስፔን ውስጥ የነበረውን የስደት ክርክር ዳግም እንዲቀሰቀስ አድርጎታል።
ከእነዚህ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ከጊዜ በኋላ ተመልሰዋል።
ይሁን እንጂ ድንበር ለመሻገር የሚቀርቡ አዳዲስ ጥሪዎች እና አሁን ባለው ከፍተኛ ጥበቃ ምክንያት በሴውታ ድንበር ላይ ዳግም ጫና እየተፈጠረ ይገኛል።
እስከዳር ግርማ
ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም
