ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ባጸደቀው መመሪያ መሠረት፤ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችን በግልጽና በብቃት ውድድር የመመደብ ሥራ ሊጀምር እንደሆነ አስታወቀ።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በአመራር ክፍተት እንዳይፈጥር ፕሬዝዳንቶች በተጠባባቂነት ሲመደቡ መቆየታቸውን ያሳወቀው ሚኒስቴሩ፤ በአዲሱ መመሪያ መሰረት የፕሬዝዳንትነት ቦታዎች ግልጽ፣ ፍትሃዊና በውድድር ላይ በተመሠረተ ሂደት እንደሚሞሉ ገልጿል።
ደረጃ በደረጃ በሚካሄደው በዚህ ውድድር፤ በመጀመሪያው ዙር ወልድያ፣ እንጅባራ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሰላሌ፣ መቱ፣ ወለጋ፣ ድሬዳዋ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ወራቤ እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲዎች ተካተዋል።
ከሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዩኒቨርሲቲዎቹ ወደ ውድድሩ እንዲገቡ ከሥራ አመራር ቦርዶቻቸው ጋር መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን፤ ሂደቱን የማስፈፀም ኃላፊነት የየዩኒቨርሲቲዎቹ ቦርዶች እንደሆነና ትምህርት ሚኒስቴር ደግሞ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም
አሥር የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሬዝዳንትነት ቦታቸውን ለግልጽ ውድድር ክፍት ሊያደርጉ ነው
