ባለሀብቶች በቲሹ ካልቸር እና በሙዝ እሴት ሰንሰለት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

የግሉ ዘርፍ በሙዝ ልማትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በስፋት እንዲሳተፍ የግብርና ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ  ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) “በሙዝ እሴት ወደ ላቀ ስኬት” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ሀገር አቀፍ የጉባኤ ላይ እንደተናገሩት፣ በዘርፉ ያለውን የቴክኖሎጂ ክፍተት ለመሙላት የባለሀብቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው።

በተለይም በ”ቲሹ ካልቸር” (Tissue culture) የችግኝ ማባዣ ዘርፍ ላይ ትልቅ የኢንቨስትመንት ክፍተት መኖሩን የጠቆሙት ሶፊያ (ዶ/ር)፣ ባለሀብቶች በዚህ ረገድ እንዲሰማሩና መንግስት አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም ወደ ዘርፉ የሚገቡ ባለሀብቶች በዙሪያቸው ካሉ አነስተኛ አርሶ አደሮች ጋር በቅንጅት በመስራት የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጥሩ አሳስበዋል።

የፋይናንስ ተቋማትም ለሙዝ አምራቾችና ላኪዎች የሚቀርበውን የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ለግብርናው ትራንስፎርሜሽን የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ይህም የሀገር ውስጥ ፍጆታን ከማሟላት ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

አዲስዓለም አበበ
ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *