መባዕ ማይክሮፋይናንስ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የተመዘገበ ቀዳሚው የማይክሮፋይናንስ ተቋም ሆነ

በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ታሪክ ውስጥ የመጀመርያው የሆነውን ምዝገባ በመፈጸም መባዕ ማይክሮፋይናንስ አክሲዮን ማህበር ቀዳሚው የማይክሮፋይናንስ ተቋም ሆኖ ተመዝግቧል።

ተቋሙ በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተቀመጡትን የህግ፣ የፋይናንስ፣ የኮርፖሬት ጎቨርናንስ እና የግልፅነት መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ በማሟላቱ ነው ይሄን ስኬት ማረጋገጥ የቻለው።

የአንድ አክሲዮን መሸጫ ዋጋ 550 የኢትዮጵያ ብር ሆኖ የተወሰነ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 110 ሚሊዮን ብር የካፒታል ማሳደጊያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ለገበያ አቅርቧል።

ይህ ስኬት መባዕ ማይክሮፋይናንስ በካፒታል ገበያው ተጨማሪ ኢንቨስትመንት በመሳብ የፋይናንስ አቅሙን አጠናክሮ አገልግሎቱን በስፋት ለማዳረስ ያስችለዋል።

በተለይም በከተማና በገጠር የሚገኙ አነስተኛ፣ ጥቃቅንና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን፣ እንዲሁም አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በስፋትና በጥራት ተዳራሽ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥርለታል።

በተጨማሪም በተቆጣጣሪው ባለስልጣን ስር መሆኑ ለነባርና ለአዳዲስ ባለአክሲዮኖች፣ ለደንበኞች እና ለቁጠባ ባለቤቶች የበለጠ አስተማማኝነትን፣ ግልፅነትንና ሙሉ ዋስትናን የሚሰጥ ነው።

ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በፋይናንስ ዘርፉ በቁጠባና ብድር አገልግሎት አዎንታዊ ተጽዕኖ ሲፈጥር የቆየው መባ ማይክሮፋይናንስ፣ ይህንን ታሪካዊ ክስተት በመጠቀም የቅርንጫፎቹን ተደራሽነት ለማስፋፋትና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር አቅዷል።

ለዓለም አሰፋ

ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *