በሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የተመራው ከፍተኛ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ልዑካን ቡድን በአሜሪካ ፔንታጎን ያካሄደውን ይፋዊ ጉብኝት ማጠናቀቁን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
በፔንታጎን የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ረዳት የመከላከያ ሚኒስትር ብራያን ጄ. ኤሊስ እና በሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የተመራው ውይይት፣ የሁለቱን አገራት ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ ደረጃ ለማሸጋገር አስችሏል ።
የስምምነቱ ማዕቀፍ ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅምንና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ፣ መተማመንን ለማጠናከር እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድና ቀጣናው ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን ያለመ ነው ተብሏል።
ሁለቱም ወገኖች የተደረሱትን ስምምነቶች በፍጥነት ወደ ተግባር በመቀየር የወደፊት አጋርነታቸውን ለማጠናከር ጽኑ ቁርጠኝነት ማሳየታቸውን ተሰምቷል።
ልዑካን ቡድኑ በቆይታው ከሌሎች የአሜሪካ መከላከያ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይቶችንና የመስክ ጉብኝቶችን ማድረጉም ተነግሯል።
ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በመከላከያ እና ደህንነት መስኮች ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ ትብብር ለመመስረት ታሪካዊ ስምምነት ላይ ደረሱ።
