በከተማዋ የኮንስትራክሽን ማዕድን ለማዉጣት የተቆፈሩ ጉድጓዶች በአልሚዎች የመልሶ ማልማት ስራ እንደማይደረግላቸዉ ተነገረ

የኮንስትራክሽን ማዕድን አልሚ ተቋማት ማዕድን ያወጡባቸዉ ቦታዎች መልሶ የማልማት ቸልተኝነት እንዳለባቸዉ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከመቶ በላይ የኮንስትራክሽን ማዕድን አልሚ ተቋማት መኖራቸዉን የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡

የኮንስትራክሽን ማዕድን አልሚዎች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት የሚያሲዙት ገንዘብ አነስተኛ መሆን ቦታዎች መልሶ ለማልማት ዳተኝነት እንደሚታይባቸዉ አድርጓል ተብሏል።

ይህንን ችግር ለመቀነስም የመልሶ ማልማት ስራዎች የአፈፃፀም መመሪያ ማዘጋጀቱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

የቁፋሮ ቦታዎቹን መልሶ ባለማልማት ምክንያት የእንስሳትን ጨምሮ ለሰዉ ህይወት መጥፋት ምክንያት እየሆነ መምጣቱ ተገልጿል።

የኮንስትራክሽን ማዕድን ማውጣት ሂደት በኋላ የሚቀሩ የተቆፈሩና የተሸረሸሩ መሬቶችን ወደ ነባር ተፈጥሯዊ ይዘታቸው መመለስና ማልማት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል፡፡

በትናንትናው ዕለት ባለስልጣኑ ከኮንስትራክሽን ማዕድን አልሚዎች ጋር በመልሶ ማልማት እና የቅድመ አደጋ መከላከል ዙሪያ ተወያይቷል።

አልሚዎች ማዕድን አውጥተው ከጨረሱ በኋላ ቦታውን የመልሶ ማልማት እና የደህንነት ስጋት እንዳይኖረዉ መስራት እያለባቸዉ ያላደረጉ ተቋማት የፍቃድ መሠረዝን ያካተተ እርምጃ እንደሚወሰድ ባለስልጣኑ ተናግሯል።

ቁምነገር አየለ

ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *