የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዘርፉን የአምስት ዓመታት የልማትና የሪፎርም ጉዞን የሚገመግምበት እና የቀጣይ የልማት ዘመን አቅጣጫዎችን የሚያስቀጥበት ሀገር አቀፍ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል፤ 1መቶ66 ቢሊየን ብር የመንግሥት የብድር ድጋፍ ለኢንተርፕራይዞች መቅረቡን እና 6መቶ23 ሺህ 26 ሄክታር መሬት ለኢንተርፕራይዞች እንዲዘጋጅ መደረጉን አብራርተዋል።
ወ/ሮ ሙፈሪያት ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ በሀገር ውስጥ 19 ሚሊየን 40 ሺህ 6መቶ39 የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውን ገልጸዋል።
ሚኒስቴሩ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት በኩልም 1 ሚሊየን 6መቶ60 ሺህ 9መቶ81 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ሚኒስትሯ አስረድተዋል።
በክህሎት ልማት ዘርፍ ደግሞ ከ20 ሚሊየን በላይ ዜጎች በአጭር ጊዜ ሥልጠና መሳተፋቸውን ገልጸዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
