በምስራቅ አፍሪካ የኃይል ቋት ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለመሆን የሚያስችል የተባለለት የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኤም ቢ ኤች ፓዎር ኩባንያ ጋር ነው የሁለትዮሽ ስምምነቱን የፈጸመው፡፡
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኢትዮ- ጅቡቲ ሁለተኛ ሰርኪዩት የማከፋፈያ ጣቢያዎችን ለመገንባትና ለማሻሻል የሚያስችለውን ስምምነት መፈራረሙን በተቋሙ የማህበራዊ ትስስር ገጽ አስነብቧል፡፡
 
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እና የኤም ቢ ኤች ፓዎር ኩባንያ የገበያና ቢዝነስ ልማት ኃላፊ ቪካሽ ኩማር በጋራ ተፈራርመውታል።
 
በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደገለጹት፤ ተቋሙ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የኃይል ትስስር በማጠናከር በምስራቅ አፍሪካ የኃይል ቋት (EAPP) ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለመሆን በትኩረት እየሰራ ይገኛል። አክለውም ይህ ፕሮጀክት ከጅቡቲ ጋር ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ይበልጥ ለማስፋፋትና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል።
 
ጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *